ቀደም ሲል ከተለያዩ ቦታ የሚመነጩ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጠበል የነበረ ሲሆን ኃይል ከማጣቱ የተነሣ ሕሙማን በሚገባ መጠበል
አይችሉም ነበር። ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ጠበሉን ከዋናው ምንጭ በማቆር እና በማጠራቀም በኃይል እንዲወርድ ተድርጓል። አሁን ምእመናን ሳይሳቀቁ በኃይል የሚወርድ ጠበል ይጠበላሉ፡፡ ሕሙማን ከተጠበሉ በኋላ በፍሳሽ መልክ የሚወርደው ማይ አይባክንም። በውኃ ማስተላለፊያ ቧንቧ ተጠልፎ ለግንባታ አገልግሎት ይውላል። በገዳሙ ውስጥ የተገነቡ እና በመገንባት ላይ ያሉት ሕንጻዎች በሙሉ በዚሁ ከጠበል በሚወርደው ውኃ በመጠቀም ነው።
