Contact Info

የውኃ ማጠራቀሚያ ገንዳ እና ቤተ መጻሕፍት

የገዳሙ ዋና ችግር የመጠጥ ውኃ ነው። ችግሩ ከፍተኛ በመሆኑ ውኃ ይቆነናል። ችግሩን
ለማቅለል የተወሰደው እርምጃ ከጠበሉ ጎን የሚመነጭ ውኃ በማጠራቀም አገልግሎት ላይ
እንዲውል ይደረጋል። ይህንንም የሚያግዝ 300,000 (ሦስት መቶ ሺህ) ሊትር የሚይዝ የውኃ ማጠራቀሚያ ገንዳ በግንብ መሬት ላይ ተገንብቶ ሥራ ጀምሯል። ከውኃ ማጠራቀሚያው ላይ የተገነባው የላይኛው ቤት 50 ሰዎችን በአንድ ጊዜ የሚያስተናግድ ዘመናዊ ቤተ መጻሕፍት እና ለገድል ማንበቢያ እንዲሆን ታስቦ የተሠራ ነው። ቤተ መጻሕፍቱም መናንያን የአብነት ተማሪዎች ጠበልተኞች እና የዕረፍት ጊዜያቸውን በገዳም የሚያሳልፉ ምእመናን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች የሚገለገሉበት ይሆናል፡፡