ገዳሙ ሲመሠረት አብሮ የተገነባው ተግባር ቤት ብዙ ዓመታት አገልግሎት በመስጠቱ አርጅቶ ወደ
መፈራረስ ተቃርቧል። አስቀድሞ ሲሠራም አካባቢውን ያገናዘበ ባለመሆኑ በጪስና በሙቀት በመታፈኑ ለተግባር ቤት አገልጋዮች ፈተና ነው፡፡ የአካባቢውን የአየር ንብረት ያገናዘበ ብዙ
አገልጋዮች ማስተናገድ የሚችል መናንያን የአብነት ተማሪዎችንና ወደ ገዳሙ የሚመጡ ምእመናን የሚያገለግል አዲስ ተግባር ቤት መሥራት አስፈልጓል። ይኅንንም ታሳቢ ያደረገ ተገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል።
