ዘመናዊ የወተት ላም እርባታ በገዳሙ በጥቂቱ የተጀመረ ሙከራ ያለ ሲሆን ይህን ተሞክሮ
ለማስፋት ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል። በዚህም 30 የፈረንጅ ላሞችን የሚይዝ ዐሥራ ዐራት በሃያ ካሬ ዘመናዊ ቤት ተገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የወተት ማቀነባበሪያም ለመገንባት በረጅም ጊዜ ዕቅድ ተይዟል። ከእነሱ በሚወጣው እበት የባዮ ጋዝ ቴክኖሎጂም የሚሠራ ይሆናል። ለዚህ ዕቅድ መሳካት ዋነኛው በቂ የውኃ አቅርቦት ሲኖር ነው፡፡ ይህንንም ችግር ለመፍታት ገዳሙ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል።
